ለስፖርት ባሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በ4ኪሎ ስፖርት ትምህርት ሥልጠና ማዕከል ሰጠ

ለስፖርት ባሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በ4ኪሎ ስፖርት ትምህርት ሥልጠና ማዕከል ሰጠ

ለስፖርት ባሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በ4ኪሎ ስፖርት ትምህርት ሥልጠና ማዕከል ሰጠ

ሀምሌ 22/2014ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ለስፖርት ባሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በ4ኪሎ ስፖርት ትምህርት ሥልጠና ማዕከል ሰጠ ።
በዚህ ሥልጠና 58 የስፖርት ባለሙያዎች እየተሳተፋበት ሲሆን የሥልጠናውም ርዕስ የስፖርት አሰተዳደርና የስፖርት በጎ ፍቃደኝነት በሚሉ ርዕሥ ሢሆን ስልጠናውን የሠጡልን የኮተቤ ዮኒቨርስቲ ሙሁር የሆኑት ዶ/ር ወንዶሰን ተፈራ ናቸው ሠልጣኞችም ከሥልጠናው ጠቃሚ ትምህርት ማግኘታቸው ገልፀው በቀጣይ ሌሎችም የግንዛቤ ማሥጨበጫ ሥልጠና ና የውይይት መድረክ እንዲዘጋጅላቸው የጠየቁ ሢሆን የፌዴሬሽኑ
ፕሬዝዳንት አቶ ቢኒያም ምሩፅ በቀጣይ ለሚመለከታቸው አካላት ጥሪ በማሥተላለፍ መድረክ አዘጋጅተን ያሉትን ጠንካራ ጎኖችና ችግሮች ላይ በመወያየት በቀጣይ ለአትሌቲክሱ እድገት በጋራ እንሠራለን በማለት ሀሣብ አቅርበዋል ።
አቶ ጎሳዬ አለማየሁ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የትምህርት ሥልጠና ዳይሬክተር የክረምት የስፖርት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ላይ የስፖርት ቤተሰቦች በየክፍለ ከተማችሁና ወረዳ ድረሥ በመውረድ ያላችሁን እውቀት በማካፈል እንዲሳተፋ እና ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውንም አስተላልፈዋል።
በስልጠናው የተሣተፉት የክለብ ቡድን መሪዎችና ስራ አስኪያጆች፣ የክፍለ ከተማ የስፖርት ፌዴሬሽን ሰብሳቢዎች፣ የክፍለ ከተማ ተወካዮች፣ የአሠልጣኝ የዳኛ ና የአንጋፋ አትሌቶች ማህበር የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚዎች እና የቴክኒክ ኮሚቴዎች ናቸው። ይህን ሥልጠና እንዲሠጥልን ባለሙያ መጋበዝና አሥፈላጊውን ዝግጅት ላደረጉልን የአ/አ/ወ/ስፖ ቢሮ የስ/ት/ሥልጠና ዳይሬክቶሬትን ከልብ እናመሠግናለን::

Recent Events

Recent News

moha-soft-drinks-industry