የፔፕሲ አዲስ አበባ ግማሽ ማራቶን ውድድር
የመጀመሪያው ፔፕሲ አዲስ አበባ ግማሽ ማራቶን ውድድር 2000 ዓ.ም ተጀመረ።
15ኛው ፔፕሲ አዲስ አበባ ግማሽ ማራቶን ውድድር
15ኛው ፔፕሲ አዲስ አበባ ግማሽ ማራቶን ውድድር ሰኔ 5 ቀን 2014 ዓ.ም መነሻውን ፒያሳ አራዳ ህንፃ እና መድረሻውን አበበ ቢቂላ ስታዲየም ውስጥ በማድረግ በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል፡፡
በ15ኛው የግማሽ ማራቶን ውድድር አሸናፊዎች፦
በወንዶች
- 1ኛ አብራራው ምስጋናው ከፌደራል ፖሊስ
- 2ኛ ደበበ ተካ ከፌደራል ማረሚያ
- 3ኛ ተሰማ መኮንን ከፌደራል ማረሚያ
- 4ኛ ፋንታሁን ሁነኛው ከንግድ ባንክ
- 5ኛ አበባው ደሴ ከፌደራል ማረሚያ
በሴቶች
- 1ኛ መሰረት ጎላ ከኢትዮ-ኤሌክትሪክ
- 2ኛ እታገኝ ወልዱ ከንግድ ባንክ
- 3ኛ ትግስት ጌትነት ከኢትዮ-ኤሌክትሪክ
- 4ኛ በርሆ አዳኖም ከንግድ ባንክ
- 5ኛ የዝናሽ ወርቅ የኔው ከፌደራል ፖሊስ
በቡድን ወንዶች ፌደራል ማረሚያ ፣ በቡድን ሴቶች ንግድ ባንክ የዋንጫ አሸናፊ ሆነዋል። በዚህ ውድድር ላሸነፉ ዋና አትሌቶች በወንድ እና በሴት፤ 1ኛ ለወጣ አትሌት 10,000 ብር፣ 2ኛ ለወጣ አትሌት 6,000 ብር፣ 3ኛ ለወጣ አትሌት 4,000 ብር፣ 4ኛ ለወጣ አትሌት 2,500 ብር፣ እና 5ኛ ለወጣ አትሌት 2,000 ብር ሽልማት ወስደዋል።
በውድድሩ ላሸነፉ አንጋፋ አትሌቶች (ከ50 ዓመት በላይ እና ከ50 አመት በታች ) 1ኛ ለወጣ አትሌት 4,000 ብር፣ 2ኛ ለወጣ አትሌት 3,000 ብር፣ እና 3ኛ ለወጣ አትሌት 2,000 ብር የገንዘብ መጠን ተረክበዋል።
15ኛው ፔፕሲ አዲስ አበባ ግማሽ ማራቶን ውድድር ተጨማሪ ምስሎች ለመመልከት ከታች ያለውን ማስፈንጠርያ ይጫኑ።
15ኛው ፔፕሲ አዲስ አበባ ግማሽ ማራቶን ውድድር
በዚህ ውድድር ላይ የተካፈሉ እስታትስቲካዊ መግለጫና የተገኙ ውጤት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

- ወንድ
- ሴት
- ድምር
በ15ኛው የፔኘሲ አዲስ አበባ የግማሽ ማራቶን ሩጫ ውድድር የክለቦች የቡድን ውጤት
ተ.ቁ | የክለቡ ስም | ያስመዘገበው ነጥብ | ደረጃ |
---|---|---|---|
1 | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ | 19 | 1ኛ |
2 | ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ | 25 | 2ኛ |
3 | ኮልፌ ቀራኒዮ | 56 | 3ኛ |
ተ.ቁ | የክለቡ ስም | ያስመዘገበው ነጥብ | ደረጃ |
---|---|---|---|
1 | ፌደራል ማረሚያ | 17 | 1ኛ |
2 | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ | 43 | 2ኛ |
3 | ፌደራል ፖሊስ | 53 | 3ኛ |
ኮከብ አሠልጣኝ በሴቶች ምድብ
1ኛ. የኢት/ንግድ ባንክ ስፖርት ክለብ አሰልጣኞች
ኮከብ አሠልጣኝ በወንዶች ምድብ
1ኛ የፌ/ማረሚያ ስፖርት ክለብ አሰልጣኞች
የ15ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ ግማሽ ማራቶን ሩጫ ውድድር የአትሌቶች የደረጃና የሰዓት ውጤት
ሰኔ 5 ቀን 2014 ዓ.ም | ፆታ ሴት | |||
---|---|---|---|---|
ተ.ቁ | የአትሌቱ ስም | የክለብ ስም | የገባበት ሰዓት | ደረጃ |
1 | መሠረት ጐሣ | ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ | 1፡13'07”08 | 1ኛ |
2 | እታገኝ ወንዱ | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ | 1፡13'18”33 | 2ኛ |
3 | ትግስት ጌትነት | ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ | 1፡14'07”02 | 3ኛ |
4 | ብርሆ አድሃና | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ | 1፡14'34”48 | 4ኛ |
5 | ዝናነሽወርቅ የኔው | ፌደራል ፖሊስ | 1፡14'42”31 | 5ኛ |
6 | መገርቱ አሰፋ | ኢትቶጵያ ንግድ ባንክ | 1፡14'53”20 | 6ኛ |
7 | ኮሬ ታምሩ | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ | 1፡14'58”92 | 7ኛ |
8 | ላቀች ግርማ | ኮልፌ ቀራኒዮ | 1፡15'17”20 | 8ኛ |
9 | ቃልኪዳን አዲሱ | ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ | 1፡15'30”48 | 9ኛ |
10 | ሠላም ፈንቴ | ኮልፌ ቀራኒዮ | 1፡15'40”90 | 10ኛ |
ሰኔ 5 ቀን 2014 ዓ.ም | ፆታ ወንድ | |||
---|---|---|---|---|
ተ.ቁ | የአትሌቱ ስም | የክለብ ስም | የገባበት ሰዓት | ደረጃ |
1 | አብራራው ምስጋናው | ፌደራል ፖሊስ | 1፡02'45”26 | 1ኛ |
2 | ደበበ ተካ | ፌደራል ማረሚያ | 1፡03'11”10 | 2ኛ |
3 | ተሰማ መኮንን | ፌደራል ማረሚያ | 1፡03'24”03 | 3ኛ |
4 | ፋንታሁን ሁነኛው | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ | 1፡03'27”81 | 4ኛ |
5 | አበባው ደቤ | ፌደራል ማረሚያ | 1፡03'35”06 | 5ኛ |
6 | ወርቁ ድረስ | አዲስ አበባ ፖሊስ | 1፡03'45”86 | 6ኛ |
7 | በቀለ ሙሉነህ | ፌደራል ማረሚያ | 1፡03'46”13 | 7ኛ |
8 | ጊዜአለው አበጀ | ኢትዮጵያ ኤሌክተሪክ | 1፡03'54”76 | 8ኛ |
9 | ገ/ጊዮርጊስ ተክሌ | ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ | 1፡04'23”01 | 9ኛ |
10 | ሞሃጅር ሀይረዲን | ፌደራል ፖሊስ | 1፡04'29”68 | 10ኛ |