አዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌደሬሽን, 40ኛው የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ጥቅምት 26/2015ዓ,ም በኢትዮጵያ ሆቴል ተካሄደ

አዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌደሬሽን, 40ኛው የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ጥቅምት 26/2015ዓ,ም በኢትዮጵያ ሆቴል ተካሄደ።
በጉባኤውም የክብር እንግዳ በመሆን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት:የስራ አሥፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እና የፅ/ቤት ተወካይና ሌሎች የሥራ ባልደረቦች የተገኙ ሲሆን በጉባኤውም የ2014 አጠቃላይ የፌዴሬሽኑ የስራ አፈፃፀም የኦዲት ሪፖርት የ2015ዓ,ም እቅድ እና የፌዴሬሽኑ የክፍያ ተመን ለውይይት ቀርቦ ተሣታፊው አሥተያየት ሠጥቶበት በማፅደቅ ፌዴሬሽኑ ለስፖርቱ ማህበረሠብ መረጃን ተደራሽ ለማድረስ የሚረዳን ድህረ -ገፅ በመክፈት ያሥመረቅን ሢሆን በተጨማሪም በ2014ዓ,ም ክለቦች ባደረጉት ተሣትፎ
- ከ1ኛ ዲቪዝዮን
1ኛ, የመቻል ክለብ 50,000ብር
2ኛ, የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች 40,000ብር
3ኛ, የኢ/ንግድ ባንክ 30,000ብር - ከ2ኛዲቪዝዮን
1ኛ አዲስ አበባ ፖሊስ 40 ,000 ብር
2ኛ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 30,000ብር
3ኛ አራዳ ክ/ከተማ 20,000ብር
3ኛ ኤልሚ ኦላንዶ 20,000ብር የተሸለሙ ሢሆን - ከአንደኛ ዲቪዝዮን ባገኙት ውጤት ወደ ሁለተኛ ዲቪዝዮን በ2013ያደጉ
ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ 20,000ብር
ኢኮስኮ 20,000ብር
በ2014 ከ2ኛ ዲቪዝዮን ወደ አንደኛ ዲቪዝዮን ላደገ ለአ/አ /ዩኒቨርስቲ 20,000ብር ድጋፍ ተሠጥቶአቸዋል። ክ/ከተሞች ክለብ ከማቋቋም አንፃር በፍጥነት ተደራጅቶ ክለብ ላቋቋመው ለለሚ ኩራ ክ/ከተማ የሞሥጋና ሠርተፍኬት ተበርክቶለታል በተጨማሪም በፌዴሬሽኑ ሥር ተመዝግበው ለሚገኙ 3 ማህበራት:-
1, የአዲስ አበባ አንጋፋ አትሌቶች ማህበር 30,000ብር
2, የአሠልጣኞች ማህበር 30,0000ብር
3, የዳኞች ማህበር 30,000 ብር ድጋፍ የተደረገላቸው መሆኑና ፌዴሬሽኑን ለብዙ አመታት ያገለገሉና ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ የሽልማትና የሠርተፍኬት ሥጦታ በመሥጠት ባማረና በደመቀ ሁኔታ ጉባኤው ተጠናቆዋል::
አዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌደሬሽን