የ39ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ የክለቦች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር በድምቀት ተካሄደ

የ39ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ የክለቦች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር በድምቀት ተካሄደ

የ39ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ የክለቦች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር በድምቀት ተካሄደ

የ39ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ የክለቦች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ሲጠናቀቅ በ1ኛ ዲቪዚዮን በሁለቱም ፆታና በአጠቃላይ አሸናፊ መከላከያ አትሌቲክስ ክለብ ፣ በ2ኛ ዲቪዚዮን በሁለቱም ፆታና በአጠቃላይ አሸናፊ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ሆነዋል። ከየካቲት 15-20 / 2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በፌዴሬሽን አዘጋጅነት በተካሄደው የክለቦች ሻምፒዮና በአንደኛ እና በሁለተኛ ዲቪዚዮን የሚገኙ 20 ክለቦች በሁለቱም ፆታ አንድ ሺህ የሚሆኑ አትሌቶች በተለያዩ ዲሲፒሊኖች ተሳታፊ ሆነው ሰንብተዋል ።

በአንደኛ ዲቪዚዮን በሁለቱም ፆታ መከላከያ ፣ በሁለተኛ ዲቪዚዮን በሁለቱም ፆታ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የዋንጫ ባለቤት ሲሆኑ በሁለቱም ዲቪዚዮንም አጠቃላይ አሸናፊ በመሆን ዋይጫ አግኝተዋል ። በአንደኛ ዲቪዚዮን መከላከያ ፣ በሁለተኛ ዲቪዚዮን አራዳ የሽብርቅ ዋንጫን አንስተዋል ። በ2ኛ ዲቪዚዮን የተሳተፈው አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ከአሸናፊነት በተጨማሪ ሪከርዶችን በመስበር ጭምር አይበገሬነቱን በውድድሩ አሳይቷል።
በ2014 ዓ.ም ሪከርድ ያሻሻሉ አትሌቶችና ኮኮብ አትሌቶች ልዩ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን ፣ ከዚህ በተጨማሪ ስፖርት ወዳዱና ስፖርተኞችን አትጊ የፌዴሬሽንኑ ምክትል ፕሬዝዳንትና የኢትዮጵያ አረንጓዴ ጎርፍ አትሌቲክ በጎ አድራጎት ድርጅት መስራችና ስራ አስኪያጅ አትሌት መልካሙ ተገኝ በግሉ ለኮኮቦቹና ሪከርድ ለሰበሩ እንዲሁም ለዳኞች 40ሺህ ብር በማውጣት የሙሉ ቱታና የገንዘብ ሽልማት በማበርከት አትሌቶችን አበረታቷል።

በፕሮግራሙ መዝጊያ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ ባደረጉት ንግግር በደማቁ ተጀምሮ በድምቀት የተጠናቀቀው የክለቦች ውድድር ሻምፒዮና መሳካት የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን በከተማ አስተዳደሩና በራሳቸው ስም አቅርበዋል። ክለቦች እንዲጠናከሩ እና ተተኪ ታዳጊዎች በጥራትና በብዛት እንዲፈሩ የጀመርነውን ስልጠና አጠናክረን እንቀጥላለን ያሉት ቢሮ ሀላፊው አቶ አብርሃም ” ዛሬ ይህን የመዝጊያ ፕሮግራም በ126ኛው የአደዋ ድላችን በዐል ዋዜማ ላይ ማካሄዳችን እንደ አባቶቻችን ጀግንነት ብዙ ጀግኖች አትሌቶችን በዐለም አደባባይ ኢትዮጵያን ያሰጠሩና እያስጠሩ በመሆናቸው እንኳን አደረሰን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።

ዐላማውን የክለቦችን ደረጃ ለመለኪያ ፣በክለቦች መካከል ብርቱ የመሸናነፍ አቅምን ለመፍጠርና እንዲሁም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በባህር ዳር ከተማ አስተናጋጅነት በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የኢትዮጵያ የክለቦች ሻምፒዮና ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን የሚወክሉ ምርጦችን መምረጫ የሆነው ውድድር ከነድምቀቱ የተጠናቀቀ መሆኑንና ለነበረው ሁሉ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ደሞ ዶክተር ትዕዛዙ ሞሴ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ፕሬዚዳንት ናችው። በሻምፒዮናው ውድድር የላቀ ተሳትፎ ለነበራቸው ክለቦች ፣ ተቋማትና ዳኞች ፌዴሬሽኑ የምስጋና ሰርተፊኬት አበርክቶላቸዋል። ፌዴሬሽኑ የ2014 ዓ.ም የ39ኛው ፔፕሲ አዲስ አበባ የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር በስኬትና በብቃት ማጠናቀቁ ታውቋል።

 

በዚህ ውድድር ላይ የተካፈሉ እስታትስቲካዊ መግለጫና የተገኙ ውጤት

Recent Events

Recent News

moha-soft-drinks-industry