1ኛው የአዲስ አበባ የአጭርና መካከለኛ የሜዳ ተግባራት ውድድር

የ2015 ዓ.ም 1ኛው የፔኘሲ አዲስ አበባ የአጭርና መካከለኛ የሜዳ ተግባራት ውድድር

1ኛው የፔኘሲ አ/አበባ የአጭርና መካከለኛ የሜዳ ተግባራት ውድድር በርካታ ተመልካች በተገኘበት በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ከሰኔ 22-24/2015 ዓ.ም በድምቀት ተከናውኗል።

የአዲስ አበባ ለአትሌቲክስ ፌድሬሽን የአዘጋጀው የ2015 የመዝጊያ ውድድር በክለቦች መካከል በሴቶችም እና በወንዶች ክፍተኛ ፍክክር ተደርጎ ፍጻሜውን አግኝቷል። ተተኪ አትሌቶች በታዩበት በዚህ ውድድር ላይ መቻል፣ኢትዮ ኤሌትሪክና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍተኛ ፉክክር አድርገዋል። በሴቶችና በወንዶች በተከናወነው በዚህ ውድድር መቻል በበላይነት ፍክክሩን አጠናቋል።

በሶስት ቀን በተረገው ውድድር አጠቃላይ ፌዴሬሽኑ ያወጣውን  የሽብርቅ መሥፈርት በማሟላት የመቻል ክለብ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኖዋል። የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ውድድሩ በሰኬት እንዲጠናቀቅ  ከፍተኛ ሥተዋፅኦ ላደረጉለት የምሥጋና እና ለተሣተፋ ክለቦች የተሣትፎ ሰርተፍኬት በመሥጥ የአመቱን የመዝጊያ ውድድር አጠናቆዋል።

ክፍለ ከተማ ወጣት                              ጾታ: ሴት

የውድድሩ ዓይነት:      6 ኪሎ ሜትር 

ደረጃ የአትሌት ስም የክለብ /ክ/ከተማ ስም
1ኛ መብራት ግደይ        ቂርቆስ  ክ/ከተማ
2ኛ ብርቱካን ይፈር      ቂርቆስ  ክ/ከተማ
3ኛ ጫልቱ አባቡ     አራዳ ክ/ከተማ
4ኛ አለምጸሀይ አስራት          አራዳ ክ/ከተማ

ክፍለ ከተማ  ወጣት                        ጾታ:  ወንድ

የውድድሩ ዓይነት:      8 ኪሎ ሜትር  

ደረጃ የአትሌት ስም የክለብ /ክ/ከተማ ስም
1ኛ ሀፍቶም አበበ        ቂርቆስ ክ/ከተማ
2ኛ አሰፋ ብርሀኑ        አራዳ ክ/ከተማ
3ኛ መረሳ ገረመው        ቂርቆስ ክ/ከተማ
4ኛ ደበሌ ጫላ     አራዳ ክ/ከተማ