የ1ኛው ሀ-18 የኢትዮጵያ ፕሮጀክቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በድሬደዋ ከተማ ያዘጋጀው የ1ኛው ሀ-18 የኢትዮጵያ ፕሮጀክቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በድሬደዋ ከተማ ያዘጋጀው የ1ኛው ሀ-18 የኢትዮጵያ ፕሮጀክቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በክልሎችና በከተማ አስተዳድሮች ውስጥ ለሚገኙ ከ18 ዓመት በታች (ሀ-18) የፕሮጀክት ሰልጣኝ አትሌቶች የውድድር እድል ለመፍጠር ብሎም ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት በሚል ከ15/06/2015 ዓ/ም እስከ 19/06/2015 ዓ/ም በድሬደዋ ከተማ ባያዘጋጀው የ1ኛው ሀ-18 የኢትዮጵያ ፕሮጀክቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌደሬሽን ከየካቲት 01-04/2015 ዓ/ም ለ4ኛ ጊዜ ካዘጋጀው የፔፕሲ አዲስ አበባ ሀ-18 የታዳጊዎች የፕሮጀክት ውድድር ላይ የተሻለ ውጤትና የተሻለ ሰዓት ያላቸውን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ ከ18 ዓመት በታች ወንድ – 12 ሴት – 14 ድምር = 26 አትሌቶች በመመልመል ለውድድር የገባን ሲሆን ከተመለመሉት አትሌቶት /ተወዳዳሪዎች/ ውስጥ በተለያየ ምክንያት 1 ወንድ እና 2 ሴት በድምሩ 3 አትሌቶች ውድድ ላይ አልተሳተፉም።

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በውድድሩ 1 የወርቅ፣ 2 የብር፣ 2 የነሐስ ሜዳሊያ በአጠቃላይ 5 ሜዳሊያዎችን ማግኘት ተችሏል። በቡድን ውጤት ከአጠቃላይ ተሳታፊዎች በሴቶች 4ኛ ደረጃ፣ በወንዶች 3ኛ ደረጃ፣ በሴቶችና በወንዶች ድምር ውጤት 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀናል፡፡

የ1ኛው የኢትዮጵያ ፕሮጀክቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር  ምስሎችን ከታች ባለው ማስፈንጠርያ ይመልከቱ።

የ1ኛው የኢትዮጵያ ፕሮጀክቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር

ተ/ቁ የውድድር አይነት /event/ ጾታ የተገኘ ውጤት ደረጃ   ውጤቱን ያስመ/ አትሌቶች ብዛት የተገኘ ሜዳሊያ
1 100 ሜትር ሴት ፍጻሜ ተወዳድረናል 4፣6 እና7ኛ 3  
ወንድ ማጣርያ ተወዳድረናል 5ኛ እና 6ኛ 2
2 200 ሜትር ሴት ፍጻሜ ተወዳድረናል 5፣6 እና 7ኛ 3  
ወንድ  ፍጻሜ ተወዳድረናል 3ኛ እና 4ኛ 2  ሮቦት ታደለ 1 ነሀስ
3 400 ሜትር ሴት ፍጻሜ ተወዳድረናል 5፣6 እና 8ኛ 2  
ወንድ ፍጻሜ ተወዳድረናል 4ኛ 1
4 800 ሜትር ሴት ፍጻሜ ተወዳድረናል 7ኛ እና 8ኛ 2  
ወንድ ፍጻሜ ተወዳድረናል 1ኛ እና 4ኛ 2  ሮቦት ታደለ 1 ወርቅ
5 1500 ሜትር ሴት ፍጻሜ ተወዳድረናል 7ኛ እና 8 2  
ወንድ ፍጻሜ ተወዳድረናል 6ተኛ 1
6 3000 ሜትር ቀጥታ ሴት ፍጻሜ ተወዳድረናል 5ኛ 1  
ወንድ ፍጻሜ ተወዳድረናል 5ኛ እና 8ኛ 2
7 2000 ሜ. መሰናክል ወንድ ፍጻሜ ተወዳድረናል 2ኛ እና 7ኛ 2 1 ብር
8 4በ400 ሜትር ድብልቅ ሪሌ ሴት/ወንድ ፍጻሜ ተወዳድረናል 2ኛ 4 1 ብር
9 ጦር ውርወራ ሴት ፍጻሜ ተወዳድረናል 3ኛ 1 1 ነሀስ
10 ርዝመት ዝላይ ሴት  ፍጻሜ ተወዳድረናል 6ኛ እና 7ኛ    
ወንድ ፍጻሜ ተወዳድረናል