26ኛው የአትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ህዳር 10/2015 ዓ.ም በአፋር ሠመራ ተካሄደ
26ኛው የአትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ህዳር 10/2015 ዓ.ም በአፋር ሠመራ ኩሪፍቱ ሪዞርት ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄዷል።
በዚህ ጉባኤ ላይ ከህ/ተ/ም/ቤት የተከበሩ ዶ/ር ቤተልሄም ላቀው እና ረ/ፕሮ/እንዳልካቸው ሌሊሳ፣ የባህልና ስ/ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል። ጉባኤው በክብርት ረ/ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የእንኳን ደህና መጣችሁ መክፈቻ ንግግር የተከፈተ ሲሆን የ25ኛው መ/ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ፀድቆ፣ የ2014 የእቅድ አፈጻጸምና የኦዲት ሪፖርት በከሰአት በፊት መርኃ ግብር ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
በ2014 ከዚህ አለም በሞት የተለዮትን ረ/ፕሮ/ በዛብህ ወልዴን የሚተካ አንድ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የማሟላትና ተጠባባቂ የነበሩት ዶ/ር ተስፋዬ አስገዶም የተተኩበት፣ የደ/ምዕ ክልል አት/ፌዴሬሽንን የአባልነት ጥያቄ መቀበልምና የክልሎችና ከተማ አስ/አትሌቲክስ ፌዴ/ አፈጻጸም ሪፖርት እንዲሁ በማለዳው ፕሮግራም ተከናውነዋል።
በከሰአት በኋላው መርኃ ግብር የ2015 በጀት አመት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን እቅድ ቀርቦ ውይይት የሚካሄድ ሲሆን፣ በ2014 የውድድር ዘመን በአትሌቲክስ ውጤታማ የሆኑ ክልሎችና ከተማ አስ/የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት ይሰጣል። የተሻሻለውን የፌዴሬሽኑን መተዳደሪያ ደንብ አቅርቦ ማጸደቅ፣ ነእድሜ ተገቢነትን የተመለከተ ጽሁፍ የሚቀርብ ይሆናል።
በጉባኤው ላይ የክልልና ከተማ አስ/ወ/ስ/ቢሮ ኃላፊዎች፣ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንቶች፣ የአትሌቲክስ ባለድርሻ አካላት፣ የክብር አባላትና ሚድያዎች ታድመዋል። ከዚህ በተጓዳኝ በሠመራ ከተማ እሁድ ህዳር 11/2015 ለሚካሄደው 18ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌይ ውድድር ቴክኒካዊ ስብሰባ ተካሂዷል።