40ኛው ፔፕሲ አዲስ አበባ ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር

40ኛው ፔፕሲ አዲስ አበባ ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ተጠናቀቀ።

ንግድ ባንክ ከ1ኛ ዲቪዚዮን በአጠቃላይ ውጤት አሸናፊ መሆን ሲችል ሲሆን አራዳ ክፍለ ከተማ ከ2ኛ ዲቪዚዮን አሸናፊ በመሆን የዎንጫ ተሸላሚ ሁነዋል።

40ኛው ፔፕሲ አዲስ አበባ ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር

 

አዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ሞሐ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክስዮን ማሕበር ጋር በመተባበር ያዘጋጅው 40ኛው ፔፕሲ አዲስ አበባ ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር በ1ኛ ዲቪዚዮን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአጠቃላይ ነጥብ በማሸነፍ ዋንጫ ሲያነሳ በ2ኛ ዲቪዚዮን አራዳ ክፍለ ከተማ በማሸነፍ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል።

የካቲት 6 2015 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ ፍጻሜውን ያገኘው 40ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ የክለቦች አትሌቲክስ ሻፒዮን 1ኛ ዲቪዚዮን በተካሄደው ፈክክር 473 ነጥብ የሰበሰበው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1ኛ፣460 ነጥብ ያስመዘገበው መቻል 2ኛ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ 350 ነጥብ በማምጣት ውድድሩን በሦስተኝነት አጠናቋል።

በአንደኛ ዲቪዚዮን በሴቶች መቻል 1ኛ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2ኛ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ 3ኛ በዚሁ ዲቪዚዮን በወንዶች ንግድ ባንክ በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ 2ኛ መቻል ሦስተኛ ሆነው ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

በሁለተኛ ዲቪዚዮን በሴት እና በወንድ ከፍተኛ ውጤት ያመጣው ኢትዮጵያ ስፓርት አካዳሚ ልዩ ተሸላሚ ሲሆን 236 ነጥብ ያስመዘገበው አራዳ ክፍለ ከተማ 1ኛ፣181 ነጥብ የሰበሰብው ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በአጠቃላይ ውጤት 2ኛ ሆኗል።

በሁለተኛ ዲቪዚዮን በሴቶች ቂርቆስ ክፍለ ከተማ 1ኛ አራዳ ክፍለ ከተማ 2ኛ ሲሆን በ2ኛ ዲቪዚዮን በወንዶች አራዳ ክፍለ ከተማ አንደኛ አዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል።

22 ክለቦች የተሳተፉበት የ2015 ፔፕሲ አዲስ አበባ ሻምፒዮን 20 ሪከርዶች የተሰበሩበት ሲሆን የሜዳ ላይ ተግባራትን ለማካሄድ የማዘውተርያ ችግር ቢያጋጥመውም በሱሉልታ በአትሌት ቀነኒሳ ማዘውተርያ ስፍራ እና በትንሿ ስቴድየም ማካሄድ መቻሉ ተገልጽዋል።

የካቲት 6 እስከ 13 2015ዓ.ም የተካሄደው 40ኛው ፔፕሲ አዲስ አበባ ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ሦስት ወርቅ ላስመዘገቡ ስፓርተኞች ለውጤታማ አሰልጣኞች ሪከርድ ለሰበሩ 20 አትሌቶች የማበረታቻ ሽልማት ሲሰጥ ለታሳታፊ ክለቦችም እውቅና መሰጠቱ ተገልጽዋል።

Recent Events

Recent News

moha-soft-drinks-industry
moha-soft-drinks-industry-pepsi-cola-mobile-1.5-litre
moha-pepsi-family-party-mobile-bottles