አራተኛው ፔፕሲ አዲስ አበባ ከ18 ዓመት በታች የታዳጊዎች ፕሮጀክት ስልጠና የአትሌቲክስ ውድድር ተካሄደ።
አራተኛው ፔፕሲ አዲስ አበባ ከ18 ዓመት በታች የታዳጊዎች ፕሮጀክት ስልጠና የአትሌቲክስ ውድድር ተካሄደ።
አዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ከሞሐ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክስዮን ማሕበር ጋር በመተባበር ያዘጋጅው 4ኛው ፔፒሲ አዲስ አበባ ከ18 አመት በታች የታዳጊ ፕሮጀክቶች ስልጠና የአሌቲክስ ውድድር ተካሄደ።
ከየካቲት 1 ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ሲያካሂድ የቆየው የታዳጊ ወጣቶች የፕሮጀክት ውድድር ፍፃሜውን አግኝቷል።
በውድድር በሴቶች አጠቃላይ ነጥብ አራዳ ክፍለ ከተማ ሲያሸንፍ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ እና አዲስ አበባ ፕሮጀክት 2ኛ እና 3ኛ ሆነው አጠናቀዋል።
በተመሳሳይ በወንዶች ውድድር አዲስ አበባ ፕሮጀክት 1ኛ ሆኖ ሲያጠያጠናቅቅ አራዳ ክፍለ ከተማ 2ኛ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውድድሩን 3ኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
በሁለቱም ፆታ ታዳጊ ወጣቶች ተተኪነታቸውን ባሳዩበት ውድድር በሜዳ ላይ ተግባራት የአጭርና መካከላኛ የርቀት ውድድሮች አሸናፊ ለሆኑ ታዳጊ አትሌቶች የወርቅ የብርና የነሐስ ሜዳልያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ጠንካራ ፋክክር በታየበት 4ኛ ፔፕሲ አዲስ አበባ የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት ውድድር 3 ወርቅና ያገኘው የአዲስ አበባ ፕሮጀክቱ አትሌት ያሬድ ነጉ የተዘጋጀለትን የሜዳሊያና የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት ከአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ዕጅ ተቀብሏል ።