የአዲስ አበባ ከተማ በ52ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር 5 ሜዳሊያዎችን በማስመዝገብ ውድድሩ በድምቀት ተጠናቋል።

የ52ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር በድምቀት ተጠናቀቀ በዚህ ውድድር ላይ የተሳተፈው አዲስ አበባ ከተማ 5 ሜዳሊያዎችን በማስመዝገብ ውድድሩን አጠናቋል።

 

የ52ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር በድምቀት ተጠናቀቀ በዚህ ውድድር ላይ የተሳተፈው አዲስ አበባ ከተማ 5 ሜዳሊያዎችን በማስመዝገብ ውድድሩን አጠናቋል።

 

ግንቦት 13/2015 ዓ.ም አዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌደሬሽን።

ከግንቦት 8 እስከ 13 ቀን 2015 ዓ.ም 52ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር በድምቀት ተካሂዷል። በዚህ ውድድር ላይ የተሳተፈው አዲስ አበባ ከተማ 5 ሜዳሊያዎችን በማስመዝገብ ውድድሩን አጠናቋል።

በሻምፒዮናው ላይ የተለያዩ ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ እና ክለቦች የተሳተፉ ሲሆን በውድድሩ ላይ ተሳትፎ ያደረገው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በ10ሺ ሜትር በሴቶች ከ1 እስከ 3ኛ በመውጣት የወርቅ፣ የብርና የነሃስ ሜዳሊያ ሲያስመዘግቡ በወንዶች በ5ሺ የብር መዳልያ ማስመዝገብ ችሏል። ከተማ አስተዳድሩ በወንዶች፣ በሴቶችም ተሳትፎ አድርጎ 1 ወርቅ፣ 2 የብር እና 1 የነሃስ ሜዳሊያ በማግኘት መልካም እንቅስቃሴ በውድድሩ አስመዝግቧል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ልማት ሚ/ር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕረዝዳን አትሌት ገዛኸኝ አበራ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ቢኒያም ምሩጽ ይፍጠር እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በክብር እንግድነት ተገኝተው ሻምፒዮናውን አድምቀውታል።

Recent Events

Recent News

moha-soft-drinks-industry
moha-soft-drinks-industry-pepsi-cola-mobile-1.5-litre
moha-pepsi-family-party-mobile-bottles