Mission

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ታሪካዊ ዳራ

ሀገራችን  ኢትዮጵያ  በኦሎምፒክ  መንደር ሰንደቅ ዓላማዋ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብና በአለም አቀፍ ደረጃ ዝናዋ ከፍ እንዲል የሚያስችላትን ምርጥ አትሌቶችን ለማፍራት  እና ስፖርቱን ለማስፋፋት መንግስት በከተማ አስተዳደሮች ፣ በክልሎች  እንዲሁም  በሀገር አቀፍ ደረጃ ፌዴሬሽኖችንን በማደራጀት  እና እውቅና በመስጠት ኃላፊነትን  በሰጠው መሰረት የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የራሱን አደረጃጀት በመፍጠር በ1974ዓ/ም የተመሰረተ ሲሆን በወቅቱ  የፌዴሬሽኑ ስራ የሚሰሩ በበጎ ፍቃደኛ የስፖርት ባለሙያዎች እና በጠንካራ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች ነበር እነዚህ ባለሙያዎች በከተማው በ11ዱም ክ/ከተማ ስፖርቱን ለማስፋፋት ስልጠናዎች በመስጠት ባለሙያዎችን በማፍራት እና የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክቶች  እንዲስፋፉ በማድረግ ውድድሮችን በማዘጋጀት ጠንካራ ክለቦችን  እንዲደራጁ አድርጎዋል፡፡ እንዲሁም በወቅቱ የነበረው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ፌዴሬሽኑ ያለበትን የበጀት ችግር ለመቅረፍና ለማሳደግ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ በተጨማሪም ውድድሮችን በማዘጋጀት የድጋፍና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ባማዘገጀት ወደ 50 ክለቦች በውድድር እንዲሳተፉ በማድረግ  ለሀገራችን ምርጥ አትሌቶችን ያፈራ እና በወቅቱ ፌዴሬሽኑ በሚያዘጋጃቸው ውድድሮች በክ/ከተማ፣ በክለቦች እና በግል የሚሳተፉ አትሌተች ከ3000 በላይ ተመዝግበው ይሳተፉ ነበር:: በወቅቱ የነበሩት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች ባደረጉት ጠንካራ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮጀከቶችን በመቅረጽ  የአዲስ አበባ ኤች አይቪ ኤድስ ጽ/ቤት እና የኢትዮጵያ  መድህን ድርጅት  ድጋፍ ያደረጉለት ሲሆን በአንደኛ ደረጃ የሞሃ ለስላሳ መጠጦች አክሲዮን ማህበር ከ1989ዓ/ም ጀምሮ ፌዴሬሽኑ በሚያደርጋቸው ውድድሮች ድጋፍ ለማድረግ ስምምነትን በመፈራረም እና ፌዴሬሽኑ እራሱን የቻለ ቢሮ እንዲኖረው በተጨማሪም ለሰራተኛው፣ ለአሰልጣኞችእና ለአትሌቶች  የመዝናኛ  ማዕከል በመገንባት ከፍተኛ ሚና የተወጣ ሲሆን በአሁኑ ሰአትም የከተማውን አትሌቲክስ  በየአመቱ በጀት በመመደብ በዋናነት የፌዴሬሽኑ ስፖንሰር  ሆኖ እየደገፈ ይገኛል፡፡

ራዕይ፣ ተልዕኮ ፣ ዋና ዋና እሴቶች Vision, Mission and Core Values

ራዕይ/Vision

ሁለንተናዊ  ስብዕናው የተሟላ በሃገር ግንባታ ሂደት ሰፊ ንቁና የተደራጀ ተሳትፎ ያለው አትሌቶችና ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ጤናማ ዜጋ፤ ብቃት ያለው ስፖርተኛና ተጠቃሚ የሆነ ህብረተሰብ በመፍጠር ቀጣይነት ባለው ልማትና ጠንካራ ሕዝባዊ መሠረት ላይ በመገንባት ፌዴሬሽኑ፤ ክለቦቻችን እና የክፍለ ከተማ ፌዴሬሽኖች ጠንካራ የሆነ የፋይና ስአቅም እዲኖራቸው ማድረግ እና ሆነው ማየት፤

ተልዕኮ/Mission

የአትሌቲክስ ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ና ማበልፀጊያ ማዕከላትን በማስፋፋት ተሰጥዖ ያላቸውን ምርጥ ስፖርተኞች ማፍራት፤

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የገቢ ምንጭ በማሻሻል የፌዴሬሽኑን ባለድርሻ አካላት ተጠቃሚነት ና እርካታ ማረጋገጥ፤

ግልፅነትና ተጠያቂነትን መሠረት ያደረገ ዘመናዊና ውጤታማ የአትሌቲክስ አስተዳደር መገንባት፤

በሳይንሳዊ ምርምር ና ጥናት ዉጤቶች በመታገዝ ጥራት ያለው የሥልጠና ና የውድድር ስርዓት በመዘርጋት ና የስነምግባር መርሆዎችን በመከተል ምርጥ ስፖርተኞችን ና አሰልጣኞችን ማፍራት፤

በተለያዩ የዕድሜ ክልል ለሚገኙ ታዳጊዎችና ወጣቶች ተደራሽ የሆነ ፍትሃዊና ማራኪ የአትሌቲክስ ውድድር ማዘጋጀት፤

የአትሌቲክስ ስፖርት በተሳትፎ በማረጋገጥ በአካልና በአእምሮ የዳበረ ጤናማና አምራች ዜጋን በማፍራት በሀገር ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁ ተወዳዳሪ የሆነ ምርጥ አትሌቶች ማፍራት ነው፡፡

ዋና ዋና እሴቶች/Core Values

የላቀ አገልግሎት መስጠት

በእውቀትና በእምነት መስራት

ቅንነት ለለውጥ ዝግጁነት

ግልጽነትንና ተጠያቂነትን እናሰፍናለን፡፡

ለውጤት እንሰራለን፣

አሳታፊነትን የተከተለ አሰራር ተግባራዊ እናደርጋለን፣

ተባብሮ መስራትን እናከብራለን፣

ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብና ብቃትያለው ስፖርተኛ ማፍራት

ደንበኞች Our Customers

አትሌቶች

የስፖርት ባለሙያዎች (አሰልጣኞች እና ዳኞች)

የስፖርት ማህበራት

ክለቦች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክፍለ ከተሞች

አንጋፋ አትሌቶች

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቢሮ አቀማመጥ እና ሁኔታ ለመመልከት ከታች የሚገኘዉን የፎቶ አልበም ይጫኑ