background image3
Shadow

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት መልዕክት

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአዲስ መልክ በማደራጀት በ11ዱም ክ/ከተሞች የአትሌቲክስ ክለብና ፕሮጀክት እንዲይዙ ለማድረግ በሰፊው የተሰራ ሲሆን በአንደኛና በሁለተኛ ዲቪዚዮን መካከል ያሉትን ክፍተቶች ለማጥበብና እኩል ተፎካካሪ ለማድረግ እንዲሁም የክለብ አደረጃጀት በአዲስ መልክ እንዲዋቀር መስፈርቶችን በማስቀመጥ ከተማ አስተዳደሩን የሚመጥኑ ክለቦችንና አትሌቶችን ለማብቃት በመስራት ላይ እንገኛለን፡፡ በተጨማሪም በከተማ አስተዳደራችን የአትሌቲክስ ስፖርትን ለማስፋፋትና ለማሳደግ ፌዴሬሽኑ ከስፖርት ቤተሰብ፣ ከባለሀብቶችና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ እየሰራን ሲሆን በ11ዱም ክ/ከተሞች የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት ስልጠና በመደገፍና በመከታተል እንዲሁም አደረጃጀት የሌላቸው ክ/ከተሞች ኮሚቴ በማደራጀት ለስፖርቱ ትኩረት በመስጠት ክለብ እንዲያቋቁሙ ከክ/ከተሞች ከፍተኛ አመራሮችና የስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር ውይይቶችን በማድረግ ቅስቀሳ እያደረግን ሲሆን ሌሎች ስፖርቱን የሚደግፉ ድርጅቶች ክለብ በመያዝ ፌዴሬሽኑ በሚያዘጋጀው አመታዊ ውድድሮች ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ አሁን ያለውን የክለቦች ተሳትፎ ቁጥር ለማሳደግ ጐን ለጐን እየሰራ ይገኛል፡፡

ፌዴሬሽኑ በአሁኑ ሰዓት ምንም ዓይነት የመንግስት በጀት ድጋፍ የማይደረግለት በመሆኑ በቀጣይ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር በመወያየት ፌዴሬሽኑ ዓመታዊ በጀት እዲደረግለት አጥብቀን የምንሰራ መሆናችን ላረጋግጥ እወዳለሁ፡፡

ላለፉት 24 ዓመታት በስፖንሰርነት እንዲሁም ከምንም በላይ የኢትዮጵያን አትሌቲክስ ለማሳደግ የጀርባ አጥንት በመሆን የሁልጊዜ አጋራችን የሆነው የሞሐ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር የፌዴሬሽኑ ህልውና በመሆን ውድድሮችን በየአመቱ እንድናደርግና የቢሮ ሰራተኞችን መቅጠር እንዲቻል ስራዎች በአግባቡ እንዲሰሩና የሙያ ማሻሻያ፣ የአሰልጣኝነትና የዳኝነት ስልጠና በመስጠት ፌዴሬሽኑ የተሻለ አደረጃጀት እንዲኖረው ከማድረጉም በላይ የነበረን ቢሮ አመቺ ባለመሆኑ ቢሮ በመከራየትና አስፈላጊውን የቢሮ ቁሳቁሶች በማሟላት ለስፖርት ቤተሰቡ አስፈላጊውን አገልግሎት እንድንሰጥ ላደረጉልን እገዛ በመላው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪና በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ስም ከፍ ያለ ምስጋናዬን ማቅረብ እወዳለሁ፡፡

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እስካሁን ያከናወናቸው ተግባራት እና የሚሰጣቸው አገልግሎት ለህብረተሰቡ ተደራሽ አልነበረም ይህን ለማሳካት ለመላው ስፖርት ወዳድ የከተማችን ነዋሪዎች የሚሰጡት አገልግሎቶች ለማሳወቅ ይህን ድህረ-ገጽ የከፈትን ሲሆን ያላችሁን አስተያየትና ድጋፍ ለአትሌቲክስ እድገት ሁሉም ባለድርሻ አካል የስፖርት ቤተሰብ፣ የመንግስት ተቋማት፣ የግል ድርጅቶች፣ ባለሀብቶች፣ በተለይም የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽንና የከንቲባ ቢሮ የራሳችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ አሳስባለሁ፡፡

አቶ ቢኒያም ምሩፅ ይፍጠር
የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት

ራዕይ/Vision

ሁለንተናዊ  ስብዕናው የተሟላ በሃገር ግንባታ ሂደት ሰፊ ንቁና የተደራጀ ተሳትፎ ያለው አትሌቶችና ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ጤና ማዜጋ ፤ብቃት ያለው ስፖርተኛና ተጠቃሚ የሆነ ህብረተሰብ በመፍጠር ቀጣይነት ባለው ልማትና ጠንካራ ሕዝባዊ መሠረት ላይ በመገንባት ፌዴሬሽኑ ፤ክለቦቻችን እና የክፍለ ከተማ ፌዴሬሽኖች ጠንካራ የሆነ የፋይና ስአቅም እዲኖራቸው ማድረግ እና ሆነው ማየት፤

ተልኮ/Mission
 • የአትሌቲክስ ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ና ማበልፀጊያ ማዕከላትን በማስፋፋት ተሰጥዖ ያላቸውን ምርጥ ስፖርተኞች ማፍራት፤
 • የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የገቢ ምንጭ በማሻሻል የፌዴሬሽኑን ባለድርሻ አካላት ተጠቃሚነት ና እርካታ ማረጋገጥ፤
 • ግልፅነትና ተጠያቂነትን መሠረት ያደረገ ዘመናዊና ውጤታማ የአትሌቲክስ አስተዳደር መገንባት፤
 • በሳይንሳዊ ምርምር ና ጥናት ዉጤቶች በመታገዝ ጥራት ያለው የሥልጠና ና የውድድር ስርዓት በመዘርጋት ና የስነምግባር መርሆዎችን በመከተል ምርጥ ስፖርተኞችን ና አሰልጣኞችን ማፍራት፤
 • በተለያዩ የዕድሜ ክልል ለሚገኙ ታዳጊዎችና ወጣቶች ተደራሽ የሆነ ፍትሃዊና ማራኪ የአትሌቲክስ ውድድር ማዘጋጀት፤
 • የአትሌቲክስ ስፖርት በተሳትፎ በማረጋገጥ በአካልና በአእምሮ የዳበረ ጤናማና አምራች ዜጋን በማፍራት በሀገር ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁ ተወዳዳሪ የሆነ ምርጥ አትሌቶች ማፍራት ነው፡፡
ዋና ዋና እሴቶች/Core Values
 • የላቀ አገልግሎት መስጠት
 • በእውቀትና በእምነት መስራት
 • ቅንነት ለለውጥ ዝግጁነት
 • ግልጽነትንና ተጠያቂነትን እናሰፍናለን፡፡
 • ለውጤት እንሰራለን፣
 • አሳታፊነትን የተከተለ አሰራር ተግባራዊ እናደርጋለን፣
 • ተባብሮ መስራትን እናከብራለን፣
 • ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብና ብቃትያለው ስፖርተኛ ማፍራት
ደንበኞች/Customers
 • አትሌቶች
 • የስፖርት ባለሙያዎች (አሰልጣኞች እና ዳኞች)
 • የስፖርት ማህበራት
 • ክለቦች
 • ክ/ከተሞች
 • አንጋፋ አትሌቶች

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ታሪካዊ ዳራ

ሀገራችን  ኢትዮጵያ  በኦሎምፒክ  መንደር ሰንደ ቃላማዋ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብና በአለም አቀፍ ደረጃ ዝናዋ ከፍ እንዲል የሚያስችላትን ምርጥ አትሌቶችን ለማፍራት  እና ስፖርቱን ለማስፋፋት መንግስት በከተማ አስተዳደሮች ፣ በክልሎች  እንዲሁም  በሀገር አቀፍ ደረጃ ፌዴሬሽኖችንን በማደራጀት  እና እውቅና በመስጠት ኃላፊነትን  በሰጠው መሰረት የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የራሱን አደረጃጀት በመፍጠር በ1974ዓ/ም የተመሰረተ ሲሆን በወቅቱ  የፌዴሬሽኑ ስራ የሚሰሩ በበጎ ፍቃደኛ የስፖርት ባለሙያዎች እና በጠንካራ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች ነበር እነዚህ ባለሙያዎች በከተማው በ11ዱም ክ/ከተማ ስፖርቱን ለማስፋፋት ስልጠናዎች በመስጠት ባለሙያዎችን በማፍራት እና የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክቶች  እንዲስፋፉ በማድረግ ውድድሮችን በማዘጋጀት ጠንካራ ክለቦችን  እንዲደራጁ አድርጎዋል፡፡

እንዲሁም በወቅቱ የነበረው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ፌዴሬሽኑ ያለበትን የበጀት ችግር ለመቅረፍና ለማሳደግ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ በተጨማሪም ውድድሮችን በማዘጋጀት የድጋፍና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ባማዘገጀት ወደ 50 ክለቦች በውድድር እንዲሳተፉ በማድረግ  ለሀገራችን ምርጥ አትሌቶችን ያፈራ እና በወቅቱ ፌዴሬሽኑ በሚያዘጋጃቸው ውድድሮች በክ/ከተማ፣ በክለቦች እና በግል የሚሳተፉ አትሌተች ከ3000 በላይ ተመዝግበው ይሳተፉ ነበር::

በወቅቱ የነበሩት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች ባደረጉት ጠንካራ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮጀከቶችን በመቅረጽ  የአዲስ አበባ ኤች አይቪ ኤድስ ጽ/ቤት እና የኢትዮጵያ  መድህን ድርጅት  ድጋፍ ያደረጉለት ሲሆን በአንደኛ ደረጃ የሞሃ ለስላሳ መጠጦች አክሲዮን ማህበር ከ1989ዓ/ም ጀምሮ ፌዴሬሽኑ በሚያደርጋቸው ውድድሮች ድጋፍ ለማድረግ ስምምነትን በመፈራረም እና ፌዴሬሽኑ እራሱን የቻለ ቢሮ እንዲኖረው በተጨማሪም ለሰራተኛው፣ ለአሰልጣኞችእና ለአትሌቶች  የመዝናኛ  ማዕከል በመገንባት ከፍተኛ ሚና የተወጣ ሲሆን በአሁኑ ሰአትም የከተማውን አትሌቲክስ  በየአመቱ በጀት በመመደብ በዋናነት የፌዴሬሽኑ ስፖንሰር  ሆኖ እየደገፈ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቢሮ አቀማመጥ እና ሁኔታ ለመመልከት ከታች የሚገኘዉን የፎቶ አልበም ይጫኑ

ከ1975 ዓ.ም ጀምሮ ፌዴሬሽኑን በፕሬዘዳንትነት እና በጽ/ቤት ኃላፊነት የመሩት

No
የቀድሞ ፕሬዘዳንት ስም
ዘመን
የወቅቱ የጽ/ቤት ኃላፊ
አስተያየት
1 አቶ ሶራ ጃርሶ 1975 – 1977 ዓ/ም
 • አቶ ግርማ አስራት
በአማተር/Volunteer
2 አቶ ግርማ አስራት 1978 – 1987 ዓ/ም
 • አቶ አበራ ዮሴፍ
በአማተር/Volunteer
3 አቶ አክሊሉ ይምታቱ 1988 – 1990 ዓ/ም
 • አቶ ታምራት ኪዳነ ወልድ
በቅጥር
4 ኮ/ር ደምሣሽ ኃይሉ 1991 – 2002 ዓ/ም
 • ታምራት ኪዳነወልድ
 • እንዳለ ጥላሁን
 • ፍቃደ ጫካ
በቅጥር
5 ዶ/ር በዛብህ ወልዴ 2003 – 2006 ዓ/ም
 • ሲሣይ ሣሙኤል
 • ፍሬዓለም ተሾመ
በቅጥር
6 አቶ ሰለሞን በቀለ 2007 – 2008 ዓ/ም
 • ገ/ሂወት ገ/ስላሴ
 • እንግዳወርቅ ዳንኤል
በቅጥር
7 ኢንጅነር ዮናስ አያሌው 2009-20011ዓ/ም
 • እንግዳወርቅ ዳንኤል
 • ነፃነት ታከለ
 • እታፈራሁ ገብሬ
በቅጥር
8 አቶ ቢኒያም ምሩፅ ይፍጠር 2011 ዓ/ም – እስከአሁን
 • እታፈራሁ ገብሬ
በቅጥር

ከ1975 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2013ዓ.ም ድረስ በአ/አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስር የተመዘገቡ ክለቦች ስም ዝርዝር በከፊል

1. ማዕከለዊ እዝ 11. ቅዱስ ጊዮርጊስ 21. አ/አበባ ዮኒቨርስቲ 31. አንበሳ ትራንስፖርት 41. ብሩህ ተስፋ
2. አየር ሐይል 12. መድህን 22. ግዮን ሆቴል 32. ፔፒሲ ኮላ 42. ዲያና
3. ኦሜድላ ፖሊስ 13. ክብረ ወሰን 23. አየር መንገድ 33. አደይ አበባ ፋብሪካ 43. ኦኔንስካነን
4. ባህር ኃይል 14. ኮ/ር ደምሣሽ ኃይሉ 24. ራስ ሆቴል 34. ከፍተኛ 25 አቃቂ 44. ፍሬ ፀጋ
5. ባንኮች 15. ኤስ አይ ኤም 25. ባህር ትራንዚት 35. አራቱ ቀጠናዎች 45. ኢትዮ ተገን
6. ኢትኮባ 16. ዮኒቲ ዮኒቨርስቲ 26. ምድር ባቡር 36. ኮስሞ ኢንጅነሪንግ 46. እንጦጦ ተራራ
7. ማረሚያ ቤቶች 17. አድማስ 27. አዲስ ጐማ 37. ኪ.ቢ.አድ ኪራይ ቤቶች 47. ሀኒ
8. አሚዲያስ 18. አዲስ ፋና 28. ደሣለች 38. ትም/ቤቶች በያዘናቸው 48. ተክሌና ልጆቹ
9. ብርታት 19. ላፍቶ አካባቢ 29. አልባ 39. አንድነት ፀረ-ኤድስ 49. የሾላ ፍሬ
10. ነጋሽ 20. የነገው ተስፋ 30. ትዕግስት ፍሬ 40. ቀስተ ደመና 50. የነገው ሰው

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ እና የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ዝርዝር

መረጃ፡

ቴክ/ኮሚቴ – ቴክኒክ ኮሚቴ

ስ/አስ/አባል – ስራ አስፈፃሚ አባል

ተ/ም/ፕሬዘዳንት – ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት

የቴክኒክ ኮሚቴና በፌደሬሽኑ ተቀጥረው የቴክኒክ ጽ/ቤትን የመሩ አካላት

No
ዘመን (ዓ.ም)
የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት
የቴክኒክ  ጸኃፊ
አስተያየት
1 ከ1975-1986 ዓ/ም በስራ አስኪያጅ ኮሚቴው ፕሬዝዳንትና በዋና ፀሐፊ የቴክኒኩ ሥራ ይከናወን ነበር (ደርበው ይሰሩ ነበር)
 • አቶ ሶራ ጃርሶ
 • አቶ ግርማ አስራት
 • በአማተር/Volunteer
 • በአማተር/Volunteer
2 1986-1990 ዓ/ም የቴክኒክ ኮሚቴ አባሎች በጐ ፍቃደኞች
 • አቶ ያሚ ከበደ
 • በአማተር/Volunteer
3 1991-2003 ዓ/ም የቴክኒክ ኮሚቴ አባሎች በጐ ፍቃደኞች
 • አቶ ግርማ አስራት
 • በአማተር/Volunteer
4 2000-2012 ዓ/ም የፌዴሬሽኑ ተቀጣሪ የቴክኒክ ኃላፊ
 • አቶ ወርቁ ስሌ
 • አቶ አንዱዓለም ያየይራድ
 • ሰለሞን አሸብር
 • የመጀመሪያው ተቀጣሪ
 • ከአ/አስ/ ኮሚሽን የተመደቡ
 • ከአ/አስ/ ኮሚሽን የተመደቡ
5 2013 ዓ/ም ጀምሮ የፌዴሬሽኑ ተቀጣሪ የቴክኒክ ኃላፊ
 • አቶ ጌታቸው ሙሉጌታ
 • ሁለተኛው ተቀጣሪ

የፌዴሬሽኑ ሰራተኞች

No
የስራ ድርሻ
ሙሉ ስም
አስተያየት
1 ጽ/ቤት ኃላፊ  

 • ወ/ሮ እታፈራሁ ገብሬ
 

 • 2011 ዓ.ም እስከ አሁን
2 የቴክኒክ ባለሙያ  

 • አቶ ጌታቸው ሙሉጌታ
 • ከ2013ዓ.ም ጀምሮ
3 ፀሐፊ  

 • ወ/ሮ ሶስና አዘነ
 • ከ2004ዓ.ም እስከ አሁን
4 የሂሳብ ባለሙያ
 • ወ/ሮ ረድኤት ከንቲባ
 • ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ
5 ገንዘብ ያዥ (ካሸር)
 • ሶሊያና አህመድ
 • ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ
6 ፅዳትና ተላላኪ
 • ክንዴነሽ ሰቦቃ
 • ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ
Google Translate »