በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስር የሚገኙት የ 1 ኛ እና 2 ኛ ዲቪዚዮን ክለቦች
የአትሌቲክስ ክለቦችና ፌዴሬሽኑ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በክፍለ ከተሞች (10 ክፍለ ከተሞች) ጋር የተዛመዱ በርካታ ክለቦችን በበላይነት ይቆጣጠራል ፡፡ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በስሩ በርካታ የአትሌቲክስ ክለብ አባላት አሉት፡፡ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ክለቦችን በበርካታ መንገዶች ይረዳል፡፡ ለምሳሌ፡ አሰልጣኞችን በማሰልጠን / የሙያ ማሻሻያ በመስጠት ፣ ውድድሮችን በማስተናገድ እና ስፖርቱን በማስተዳዳር ፣ ወዘተ የመሳሰሉ መንገዶች ይረዳል ፡፡
የአትሌቲክስ ክለቦች
የአትሌቲክስ ክለቦች ሁለተኛው የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ተቋማዊ ቁልፍ ተዋናዮች ናቸው፡፡ ከአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና ከሌሎቹ የስፖርት ተቋማት ጎን ለጎን ለአትሌቶች ሥልጠናና አመራር ይሰጣሉ፡፡
የአንደኛና ሁለተኛ ዲቪዚዮን ክለቦች
በአዲስ አበባ የሚገኙት የአትሌቲክስ ክለቦች በአንደኛና በሁለተኛ ዲቪዚዮን ክለቦች የተከፋፈሉ ናቸው፡፡
የአትሌቲክስ ክለቦቹም የሚከተሉት ናቸዉ፡
አንደኛ ዲቪዚዮን
ተራ ቁጥር | የክለቡ ስም | የተቋቋመበት ዓ.ም | ዲቪዚዮን |
1 | መከላከያ | 1936 | አንደኛ |
2 | ፌደራል ፖሊስ | 1940 | አንደኛ |
3 | ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ | 1953 | አንደኛ |
4 | ፌደራል ማረሚያ | 1975 | አንደኛ |
5 | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ | 1975 | አንደኛ |
6 | ኢ.ኮ.ስ.ኮ | 1993 | አንደኛ |
7 | ኮልፌ ቀራንዮ | 2010 | አንደኛ |
ሁለተኛ ዲቪዚዮን
ተራ ቁጥር | የክለቡ ስም | የተቋቋመበት ዓ.ም | ዲቪዚዮን |
1 | ኢትዮ ተገን | 1993 | ሁለተኛ |
2 | ተክሌና ልጆቹ | 1998 | ሁለተኛ |
3 | ጌታ ዘሩ | 1998 | ሁለተኛ |
4 | አይሽዓ | 1998 | ሁለተኛ |
5 | ወጣቶች አንድነት | 2000 | ሁለተኛ |
6 | ካራማራ | 2010 | ሁለተኛ |
7 | አ/አበባ ዮኒቨርስቲ | 2004 | ሁለተኛ |
8 | ኮስሞ ኢንጅነሪንግ | 2004 | ሁለተኛ |
9 | ሀበሻ አትሌቲክስ | 2007 | ሁለተኛ |
10 | ኢትዮ ካርል | 2007 | ሁለተኛ |
11 | ራን አፍሪካ | 2008 | ሁለተኛ |
12 | ኤልሚ ኦሊንዶ | 2008 | ሁለተኛ |
13 | አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን | 2011 | ሁለተኛ |
14 | አራዳ | 2011 | ሁለተኛ |
15 | ዳሎል | 2012 | ሁለተኛ |