Photo Collection1

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ታሪካዊ ዳራ

ሀገራችን ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ መንደር ሰንደቅ ዓላማዋ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብና በአለም አቀፍ ደረጃ ዝናዋ ከፍ እንዲል የሚያስችላትን ምርጥ አትሌቶችን ለማፍራት እና ስፖርቱን ለማስፋፋት መንግስት በከተማ አስተዳደሮች ፣ በክልሎች እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ፌዴሬሽኖችንን በማደራጀት እና እውቅና በመስጠት ኃላፊነትን በሰጠው መሰረት የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የራሱን አደረጃጀት በመፍጠር በ1974ዓ/ም የተመሰረተ ሲሆን በወቅቱ የፌዴሬሽኑ ስራ የሚሰሩ በበጎ ፍቃደኛ የስፖርት ባለሙያዎች እና በጠንካራ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች ነበር እነዚህ ባለሙያዎች በከተማው በ11ዱም ክ/ከተማ ስፖርቱን ለማስፋፋት ስልጠናዎች በመስጠት ባለሙያዎችን በማፍራት እና የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክቶች እንዲስፋፉ በማድረግ ውድድሮችን በማዘጋጀት ጠንካራ ክለቦችን እንዲደራጁ አድርጎዋል፡፡

እንዲሁም በወቅቱ የነበረው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ፌዴሬሽኑ ያለበትን የበጀት ችግር ለመቅረፍና ለማሳደግ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ በተጨማሪም ውድድሮችን በማዘጋጀት የድጋፍና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ባማዘገጀት ወደ 50 ክለቦች በውድድር እንዲሳተፉ በማድረግ ለሀገራችን ምርጥ አትሌቶችን ያፈራ እና በወቅቱ ፌዴሬሽኑ በሚያዘጋጃቸው ውድድሮች በክ/ከተማ፣ በክለቦች እና በግል የሚሳተፉ አትሌተች ከ3000 በላይ ተመዝግበው ይሳተፉ ነበር::

በወቅቱ የነበሩት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች ባደረጉት ጠንካራ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮጀከቶችን በመቅረጽ የአዲስ አበባ ኤች አይቪ ኤድስ ጽ/ቤት እና የኢትዮጵያ መድህን ድርጅት ድጋፍ ያደረጉለት ሲሆን በአንደኛ ደረጃ የሞሃ ለስላሳ መጠጦች አክሲዮን ማህበር ከ1989ዓ/ም ጀምሮ ፌዴሬሽኑ በሚያደርጋቸው ውድድሮች ድጋፍ ለማድረግ ስምምነትን በመፈራረም እና ፌዴሬሽኑ እራሱን የቻለ ቢሮ እንዲኖረው በተጨማሪም ለሰራተኛው፣ ለአሰልጣኞችእና ለአትሌቶች የመዝናኛ ማዕከል በመገንባት ከፍተኛ ሚና የተወጣ ሲሆን በአሁኑ ሰአትም የከተማውን አትሌቲክስ በየአመቱ በጀት በመመደብ በዋናነት የፌዴሬሽኑ ስፖንሰር ሆኖ እየደገፈ ይገኛል፡፡

አ/አ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በፕሬዘዳንትነት - ከ1975 ዓ.ም ጀምሮ የመሩ

ዓመተ ምህረት የወቅቱ ፕሬዝዳንት የወቅቱ የጽ/ቤት ኃላፊ
1975 – 1977 ዓ/ም አቶ ሶራ ጃርሶ አቶ ግርማ አስራት
1978 – 1987 ዓ/ም አቶ ግርማ አስራት አቶ አበራ ዮሴፍ
1988 – 1990 ዓ/ም አቶ አክሊሉ ይምታቱ አቶ ታምራት ኪዳነ ወልድ
1991 – 2002 ዓ/ም ኮ/ር ደምሣሽ ኃይሉ አቶ ታምራት ኪዳነ ወልድ፣
አቶ እንዳለ ጥላሁን፣
አቶ ፍቃደ ጫካ
2003 – 2006 ዓ/ም ዶ/ር በዛብህ ወልዴ አቶ ሲሣይ ሣሙኤል፣
አቶ ፍሬዓለም ተሾመ
2009-20011ዓ/ም ኢንጅነር ዮናስ አያሌው አቶ እንግዳወርቅ ዳንኤል፣
አቶ ነፃነት ታከለ፣
ወ/ሮ እታፈራሁ ገብሬ
2012 – እስከአሁን አቶ ቢኒያም ምሩፅ ይፍጠር ወ/ሮ እታፈራሁ ገብሬ

አ/አ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በቴክኒክ ባለሙያነት - ከ1975 ዓ.ም ጀምሮ የመሩ

ዓመተ ምህረት የወቅቱ የቴክኒክ ባለሙያ
ከ1975-1986 ዓ/ም አቶ ሶራ ጃርሶ
አቶ ግርማ አስራት
1986-1990 ዓ/ም አቶ ያሚ ከበደ
1991-2003 ዓ/ም አቶ ግርማ አስራት
2000-2012 ዓ/ም አቶ ወርቁ ስሌ
አቶ አንዱዓለም ያየይራድ
ሰለሞን አሸብር
2013 - 2014 ዓ/ም አቶ ጌታቸው ሙሉጌታ
2014 ዓ/ም ጀምሮ አቶ ደረጄ የኔአባት
አቶ ስንታየሁ መለሰ

ውድድሮች የተጀመረበት ዓመትና የውድድሮቹ ዓይነት

ተ.ቁ ዘመን (ዓ.ም) የውድድሩ ስም ተሳታፊዎች
1 1975 ዓ.ም የአዲስ አበባ ክለቦች አትሌቲክስ ሻምፒዮና 50 ክለቦች፣ተቋማት፤ት/ቤቶች፣ዞኖች እና ወረዳዎች
2 1976 ዓ.ም የመጀመሪያው የአ/አበባ ሀገር አቋራጭ ውድድር በሳንሱሲ(ገፈርሳ)  
3 ጥር 22/1986ዓ.ም በአ/አበባ ስታዲየም በእግር ኳስ ውድድር ጣልቃ የአዲስ አበባ ክለቦች ከ100ሜትር እስከ 3000ሜ
4 1988 ዓ.ም የመጀመሪያው የአ/አበባ ማራቶን ሪሌ ውድድር በአ/አበባስ ታዲየም ዙር ያተጀመረ ከ13 ክለቦች የተውጣጡ 91 ወንድ ተወዳዳሪዎች
5 ታህሳስ 27/1989ዓ/ም የመጀመሪያው የአ/አበባ ማራቶን ውድድር  -መነሻና መድረሻው አዲስ አበባ ስታዲየም 9 ክለቦች በወንዶች እና 5 ክለቦች በሴቶች 278 እና በሴት 26 አትሌቶች
6 ከ1993ዓ.ም-1998ዓ.ም ኤች.አይ.ቪ ኤድስን ለመከላከልና ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተደረገ ውድድር (በአዲስአበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት) አ/አበባ ያሉ ከለቦችና ክልሎች በዝዋይ ከተማ፣ቤንሻንጉል፣ሀረር፣አርባምንጭ፣ትግራይ፣ ጎንደር
7 ከ1995-2000ዓ.ም የኢትዮጵያ መድህን የ10ኪ.ሜ የጎዳና ሩጫ መነሻና መድረሻው ለገሃር መድህን ዋና መስሪያ ቤት የአዲስ አበባ ክለቦች
8 2000 ዓ.ም የመጀመሪያው የአ/አበባ ግማሽ ማራቶን ውድድር ተጀመረ

ራዕይ፣ ተልዕኮ ፣ ዋና ዋና እሴቶች Vision, Mission and Core Values

ራዕይ/Vision

ሁለንተናዊ  ስብዕናው የተሟላ በሃገር ግንባታ ሂደት ሰፊ ንቁና የተደራጀ ተሳትፎ ያለው አትሌቶችና ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ጤናማ ዜጋ፤ ብቃት ያለው ስፖርተኛና ተጠቃሚ የሆነ ህብረተሰብ በመፍጠር ቀጣይነት ባለው ልማትና ጠንካራ ሕዝባዊ መሠረት ላይ በመገንባት ፌዴሬሽኑ፤ ክለቦቻችን እና የክፍለ ከተማ ፌዴሬሽኖች ጠንካራ የሆነ የፋይና ስአቅም እዲኖራቸው ማድረግ እና ሆነው ማየት፤

ተልዕኮ/Mission

የአትሌቲክስ ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ና ማበልፀጊያ ማዕከላትን በማስፋፋት ተሰጥዖ ያላቸውን ምርጥ ስፖርተኞች ማፍራት፤

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የገቢ ምንጭ በማሻሻል የፌዴሬሽኑን ባለድርሻ አካላት ተጠቃሚነት ና እርካታ ማረጋገጥ፤

ግልፅነትና ተጠያቂነትን መሠረት ያደረገ ዘመናዊና ውጤታማ የአትሌቲክስ አስተዳደር መገንባት፤

በሳይንሳዊ ምርምር ና ጥናት ዉጤቶች በመታገዝ ጥራት ያለው የሥልጠና ና የውድድር ስርዓት በመዘርጋት ና የስነምግባር መርሆዎችን በመከተል ምርጥ ስፖርተኞችን ና አሰልጣኞችን ማፍራት፤

በተለያዩ የዕድሜ ክልል ለሚገኙ ታዳጊዎችና ወጣቶች ተደራሽ የሆነ ፍትሃዊና ማራኪ የአትሌቲክስ ውድድር ማዘጋጀት፤

የአትሌቲክስ ስፖርት በተሳትፎ በማረጋገጥ በአካልና በአእምሮ የዳበረ ጤናማና አምራች ዜጋን በማፍራት በሀገር ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁ ተወዳዳሪ የሆነ ምርጥ አትሌቶች ማፍራት ነው፡፡

ዋና ዋና እሴቶች/Core Values

የላቀ አገልግሎት መስጠት

በእውቀትና በእምነት መስራት

ቅንነት ለለውጥ ዝግጁነት

ግልጽነትንና ተጠያቂነትን እናሰፍናለን፡፡

ለውጤት እንሰራለን፣

አሳታፊነትን የተከተለ አሰራር ተግባራዊ እናደርጋለን፣

ተባብሮ መስራትን እናከብራለን፣

ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብና ብቃትያለው ስፖርተኛ ማፍራት