የስራ ላይ ልምድ ልውውጥ ከአ/አ ጅምናስቲክ፣ ውሃ ዋና እና ጠ/ቴኒስ ፌዴሬሽን

የስራ ላይ ልምድ ልውውጥ ከአ/አ ጅምናስቲክ፣ ውሃ ዋና እና ጠ/ቴኒስ ፌዴሬሽን

መጋቢት 26/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ጅምናስቲክ ፌዴሬሽን፣ ውሃ ዋና እና ጠ/ቴኒስ ፌዴሬሽን ከአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር የስራ ላይ ልምድ ልውውጥ ያደረጉ ሲሆን በልምድ ልውውጥ የታዩ የመረጃ አያያዝ፣ የከለቦች፣ የማህበራትና የኮሚቴ አደረጃጀት፣ የሀብት አሰባሰብ የታዳጊ ወጣቶች ሥልጠና፤ ከብሄራዊ ፌዴሬሽን እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ፌዴሬሽኑ ያለው ግንኙነት፣ የቢሮ አደረጃጀት እና ሌሎችም የሥራ ልምድ ልውውጥ ተደርጓል። በልምድ ልውውጡ የፌዴሬሽኖቹ ፕሬዝዳንት እና ስራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም የየፌዴሬሽኖች ጽ/ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል ። በልምድ ልውውጡም ከአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በርካታ ልምዶችን ያገኙ መሆናቸውን ለፌዴሬሽኑ ገልፀዋል።