የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ከፌድሬሽኖችና ስፖርት ማህበራት ጋር የተሞክሮ ልውውጥ አደረገ

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ከፌድሬሽኖችና ስፖርት ማህበራት ጋር የተሞክሮ ልውውጥ አደረገ

 

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ከፌድሬሽኖችና ስፖርት ማህበራት ጋር የተሞክሮ ልውውጥ አደረገ።

 

ሰኔ 8/2015 ዓ.ም  አዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌድሬሽን።

 

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ከፌድሬሽኖችና ስፖርት ማህበራት  ጋር የተሞክሮ ልውውጥ አደረገ።

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ባዘጋጀው የምርጥ ተሞክሮ የልምድ  ልውውጥ ላይ የተገኙት ባለድርሻዎች አካላት  በፌድሬሽኑ ስራ መደመማቸውን ገልጸዋል። ፌድሬሽኑ ከፍተኛ ስራ መስራቱን የገለጹት ተሳታፊዎች ለሌሎች ተቋማት እንደሞዴል ሊወሰድ የሚገባው ነው ብለዋል።

ፌድሬሸኑ ባለፋት አራት አመታት ባደረገው ጠንካራ ስራ ከቢሮ አደረጃጅት ጀምሮ ከፍተኛ ለውጥ ማስመዝገቡን የገለጹት የፌድሬሽኑ ፕረዝደንት አቶ ቢኒያም ምሩጽ ይፍጠር ናቸው። አቶ ቢኒያም አያይዘውም የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌድሬሽኑን ስንረከብ ውስን የሰው ኃይልና የፋይናንስ ስርዓት እንደነበረ በመጥቀስ  የነበሩ ክፍተቶችን በመሞላት ውጤታማ ሁነናል ብለዋል።

በቴክኒኩ ረገድ ከፍተኛ ስራ እንደተሰራ የገለጹት ደግሞ የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢው አትሌት ተሰማ አብሽሮ ናቸው። አትሌት ተሰማ ውድድር ስልጠና ላይ ትኩረት ያደረጉ ሰራዎች በተግባር እንደተሰሩ እና ፌድሬሽኑ ከመቸውም ጊዜ በላይ  በመግባባት ሁሉን አቀፍ ስራ የተሰራበት እንደነበረ ነው አትሌት ተሰማ አብሽሮ የተናግሯል።

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌድሬሽን የጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ እታፈራሁ ገብሬ በበኩላቸው የፌድሬሽኑን ተሞክሮ ሲያቀርቡ ከፍተኛ አፈጻጽም እንደተከናወነ ጠቅሰዋል። በታዳጊ ወጣቶች ላይ አመርቂ ስራ ከመሰራቱም ባሻገር ከብሔራዊ ፌድሬሽኑ ጋር ትስስር በመፍጠር ሁሉን አቀፍ ስራ መሰራቱን ለተሳታፊዎች አሳይተዋል።

ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ የሰጡት  አቶ ቢኒያም ደግሞ ፌድሬሽኑ ከሞሐ ጋር በገባው ውል ከፍተኛ ገቢ ማስገባቱን በመግለጽ ፌድሬሽን ገቢውን ከስፖንሰር ብቻ ሳይሆን ከውድድር ፈቃድና መሰል ኩነቶች ጭምር መሰብሰቡን በመጥቀሰ በተለያዩ ምክንያቶች ውድድር ማድረግ ባንችልም በ2015 ዓ.ም መልካም እንቅስቃሴ የታየበት ነበር ብለውል።

Recent Events

Recent News

moha-soft-drinks-industry
moha-soft-drinks-industry-pepsi-cola-mobile-1.5-litre
moha-pepsi-family-party-mobile-bottles