የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት የስራ ጉብኝት

የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት የስራ ጉብኝት ተደረገ

ሰኔ 29/2015 ዓ.ም አዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

የአዲስ አበባ ከተማ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በጋራ በመሆን ከከፈቷቸው የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት አንዱ የሆነውን የጃንሜዳ ፕሮጀክት ጣቢያ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከመጡ ከፍተኛ ዳይሬክተሮች እና በአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት የተመራ ስራ አስፈፃሚዎች እና ጽ/ቤት ኃላፊ እንዲሁም የቴክኒክ ኮሚቴዎች በተገኙበት ምልከታ በትንሿ ስታዲየም ተደረገ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሰኔ29-30/2015 ጀምሮ በፌዴሬሽናችን የውሥጥ አሠራር በጃንሜዳ እና በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚሠለጥኑ የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት የሥልጠና ሂደት እና ክለቦች ያሉበትን ደረጃ በማየት መስተካከል ያለባቸውን እንድናሥተካክል  እና እየተሠሩ ያሉ ውጤታማ ሥራዎችን በማበረታታ ድጋፍና ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ። ይህ ድጋፍና ክትትል  የፊታችን ሰኞና ማክሰኞ የሚቀጥል ይሆናል።