ከክለቦች ጋር የተካሄደ አጠቃላይ ውይይት

ከክለቦች ጋር የተካሄደ አጠቃላይ ውይይት

ሚያዝያ 19/2015 ዓ.ም

ሚያዝያ 19/2015 ዓ.ም አጠቃላይ በተካሄዱ ውድድሮችና ባልተካሄዱ ውድድሮች ላይ ከክለቦች ጋር ውይይት አድርጎዋል። በዚህም ውይይት ለቀጣይ መሥተካከል ያለበት ጉዳዮች የተቀበልን ሢሆን የማራቶንና የግማሽ ማራቶን ውድድር አለመካሄዱ አትሌቶች የተጎዱበት መሆኑን ክለቦች የገለፁ ሲሆን ነገር ግን በውይይቱ ላይ በቀረበው መሠረት ውድድሩ ያልተካሄደበት ምክንያቶች አሣማኝ በመሆናቸው የማራቶን ውድድር ከዚህ በኋላ ማድረግ እንደማይቻል ነገር ግን የግማሽ ማራቶን ውድድር ከኢትዮጵያ ሻፒዮና በኋላ ብናካሂድ የሚል ሀሣብ የተነሣ ሢሆን ክለቦችም አትሌቶቹ ተዘጋጅተው አጉል እንዳይሆኑ በመጀመሪያ ፌዴሬሽኑ ፍቃድ ማግኘቱ ሲያረጋግጥ ጠርቶ ቢያወያየን የሚል ሀሣብ ሰጥቶዋል። የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ውድድር ላይ አዲስ አበባን የሚወክሉ አትሌቶች ክለቦች በደንቡና መመሪያ መሠረት መሥጠት አለባችሁ በሚለው ሀሣብ ላይም የተወያየን ሲሆን ለዚህም ፌዴሬሽኑ በደብዳቤ የሚፈልጋቸውን አትሌቶች ለይቶ ለክለቦች ያቅርብና ክለቦች መልሥ እንዲሠጡበት ቢደረግ የሚል ሀሣብ ቀርቦዋል። በመጨረሻም ከተማ አሥተዳደሩ ሚያዝያ 22/2015 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ ባዘጋጀው ስፖርታዊ ንቅናቄ ፕሮግራም ላይ አትሌቶቻቸውና አሠልጣኞች ከማለዳው 12:00 ጀምሮ እንዲገኙ ሁሉም የተሠጠውን ኃላፊነት እንዲወጣና ለፕሮግራሙ ሥኬት አሥፈላጊውን ጥሪ እንዲያደርግ ማሣሠቢያ ተሠጥቶዋል።