የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደ።
ነሀሴ 28/2015 ዓ.ም አዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
👉የአዲስ አበባ ዳኞች ማህበር ነሀሴ 28/2015 ዓ.ም በአራት ኪሎ ስፖርት ማእከል አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደ በጉባኤውም የተገኙ የክብር እንግዶች የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት፣ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ም/ፕሬዝዳንት፣ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ አሠልጣኞች ማህበር ተወካይ፣ የአዲስ አበባ አንጋፋ አትሌቶች ማህበር ተወካይ እና የዳኞች ማህበር አባላት ተገኝተዋል::
👉አጀንዳዎችም:-
– የ2014 ዓ.ም ቃለ-ጉባዬ
– የ2015 ዓ.ም አፈጻጸም ሪፖርት
– የ2015 ዓ.ም የፋይናስ ሪፖርት
– የ2016 ዓ.ም እቅድ ሢሆኑ ለጉባዬው ቀርቦ አሥተያየት ከተሠጠበት በኋላ በማፅደቅ የአመቱ ጠቅላላ ጉባኤ የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታሁን ለአለም ለማህበሩ ድጋፍ ያደረጉላቸውን በሙሉ በማመሥገን የማጠቃለያ ንግግር አድርገዋል::