የአጭር እርቀት የአትሌቲክስ ውድድር በ10ት/ቤቶች መካከል

የአጭር እርቀት የአትሌቲክስ ውድድር በ10ት/ቤቶች መካከል

መጋቢት 24/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሶፊ ማልት ጋር በመተባበር በ10ት/ቤቶች መካከል  የአጭር እርቀት የአትሌቲክስ ውድድር መጋቢት 23/2015ዓ,ም በአበበ ቢቂላ ስታዲዮም ማካሄድ ጀመረ  የዚህ ውድድር አላማ  በቀጣይ  ፌዴሬሽኑ  የሚያዘጋጀው  የት/ቤት  ውድድር ተጨማሪ  በማድረግ በውድድሩ  ውጤታማ የሆኑትን ታዳጊ ወጣቶችን  በመለየት   በአንድ  ላይ በማሠባሠብ ሥልጠና  በመሥጠት  ለ2016ዓ .ም ለሚካሄደው ከ18በታች የታዳጊ ወጣቶች ውድድር ከተማ አስተዳደሩን  የሚወክሉ  አትሌቶችን  ዝግጁ ለማድረግ  ፌዴሬሽኑ አቅዶዋል::

የሶፊ ማልት የተማሪዎች ውድድር ዛሬ መጋቢት 24/2015ዓ/ም የቦሌ መድሃኒያለም መሠናዶ ት/ቤት 1ኛ በመውጣት የ50ሺ ብርና የዋንጫ ተሸላሚ ሢሆን በ2ኛ ደረጃ የቦሌ ማህረሠብ ትቤ/ት እና 3ኛ የአዲስ ከተማ ት/ቤት የዋንጫተሸላሚ ሆነዋል::በተጨማሪም ለተማሪዎች የሚሆን አጋዥ መፅሀፎች የተሸለሙ ሢሆን በየውድድሩ የወርቅ መዳሊያ ላሥመዘገቡ ተማሪዎች 2000ብር በመሸለም ውድድሩ ተጠናቋል።

sofi1
sofi2
sofi3