የልምድ ልውውጥ ከክልል አትሌቲክስ ፌደሬሽን

ከክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የልምድ ልውውጥ

ግንቦት 15/2015 ዓ.ም

የፌዴሬሽኑ ስራ አሥፈፃሚ ኮሚቴ የቴክኒክ ኮሚቴና የሥልጠና እና የውድድር ዘርፍ የቴክኒክ ባለሙያዎች ከግንቦት 15- 18/2015ዓ,ም በደቡብ በሲዳማና በኦሮምያ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን  የልምድ ልውውጥ  አድርገዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሲዳማ እና ከደቡብ ክልላዊ መንግሥት አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር የስራ ላይ ልምድ ልውውጥ ከግንቦት 15-17/2015 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ እና በአርባ ምንጭ ከተማ ሢያካሂድ የቆየው በማጠናቀቅ ግንቦት 8/2015 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ የተመለሠ ሢሆን የልምድ ልውውጡ መጨረሻ በአርባ ምንጭ የሚገኘው ከ18 አመት እድሜ በታች የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት ሠልጣኞችን የጎበኘ መሆኑና በአጠቃላይ ከሁለቱም ክልል ከአደረጃጀት፣ ከአሰራር፣ ከሀብት አሰባሰብ፣ ከስልጠና እና በውድድር ዙሪያ መልካም ተሞክርዎችን ያገኘን ሲሆን በቀጣይ አብሮ ለመስራትና ለመደጋገፍ በመወያየት የአጠናቀቅን ሢሆን ሁለቱም ክልሎች ላደረጉልን አቀባበልና መሥተንግዶ በፌዴሬሽኑ ከፍተኛ ምሥጋና ያቀርባል።