background image3
background image3
previous arrow
next arrow

በአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሚደገፉ የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት

Tadagiwoch AA (2)

አዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በጋራ በመሆን ከከፈታቸው የታዳጊ ወጣቶች አትሌቲክስ ፕሮጀክት ጣቢያዎች አንዱ የሆነው የጃንሜዳ ፕሮጀክት ጣቢያ በሥልጠና ላይ ሆነው የሚያሣይ ሢሆን እነዚህ ታዳጊዎች በድሬዳዋ ላይ በተካሄደው የ1ኛው የታዳጊ ወጣቶች ውድድር ላይ ከተማ አሥተዳደሩን በመወከል ከክልሎች 3ኛ ደረጃ በመውጣት ያጠናቀቁ ሢሆን ከነዚህ ታዳጊ ወጣቶች ውሥጥ ሀገርን በመወከል በዛምቢያ በተካሄደው የታዳጊ ወጣቶች ውድድር ላይ በ800ሜ ለከተማ አሥተዳደሩ ድሬዳዋ ላይ በተካሄደው ውድድር የወርቅ መዳሊያ ያሠመዘገበው አትሌት ሮቤል በመሣተፍ 4ኛ በመውጣት ውድድሩን ያጠናቀቀ መሆኑ ለነዚህ ታዳጊ ወጣቶች ትልቅ ተሥፋ የሠጠ ሆኖዋል።

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ያደረገለትን ትጥቅ ድጋፍ ለታዳጊ ወጣቶች ወላጆች በተገኙበት የአመቱን የሥልጠና ሂደት በጋራ ከገመገመ በኋላ ለታዳጊ ወጣቶች የትጥቅ ርክክብ አድርገዋል።

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሚደገፍ የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት

የአዲስ አበባ ታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ፕሮጀክት

በዚህ ፕሮጀክት ዉስጥ ከ18 እና ከ15  ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊ ወጣቶች ስልጠና የሚወስዱ ሲሆን ስልጠናቸዉንም ሲያጠናቅቁ ፌዴሬሽኑ ውድድር በማድረግ ብቁ የሆኑ አትሌቶችን በመምረጥ በአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተይዘው ድጋፍና ክትትል እንዲሁም ስልጠና ይሰጣቸዋል፡፡

ታዳጊዎች 2013

ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በየአመቱ የስፖርት ልብስና የወተት ድጋፍ እየተሰጣቸው ከአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በጀት ሁለት አሠልጣኞችን በመቅጠር ና ለታዳጊ ወጣቶች በወር 250ብር አበል በመክፈል ክትትልና ድጋፍ የሚደረግላቸው የፕሮጀክት ሠልጣኞች ናቸዉ፡፡