የአዲስ አበባ ከተማ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ውጤት ላስመዘገቡ አትሌቶች የማበረታቻ ሽልማትና ዕውቅና ሰጠ።

የአዲስ አበባ ከተማ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ውጤት ላስመዘገቡ አትሌቶች የማበረታቻ ሽልማትና ዕውቅና ሰጠ።

አዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

 

የአዲስ አበባ ከተማ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ውጤት ላስመዘገቡ አትሌቶች የማበረታቻ ሽልማትና ዕውቅና ሰጠ።

 

ሰኔ 15/2015 ዓ.ም አዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

 

የአዲስ አበባ ከተማ አትሌቲክስ ፌድሬሽን አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ወክለው በ52ኛው ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እና በ1ኛው የታዳጊዎች ውድድር ውጤት ለስመዘገቡ አትሌቶች የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት እና እውቅና ሰጠ።

በእውቅና ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ማህበራት ማደራጃና ውድድር ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አያሌው ታደለ ፌዴሬሽኑ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት እያከናወነ ያለውን ዘረሸፍ ብዙ ተግባር አድንቀው ከተማ አስተዳደሩን በተለያዩ ውድድሮች ወክለው ውጤት የመጡ ስፖርተኞችን ፌዴሬሽኑ እውቅና መስጠት ደግሞ የሚበረታታ ተግባር ነው ብለዋል።

አቶ አያሌው በቀጣይ የታዳጊ ወጣቶች የፕሮጀክት ጣቢያዎችን ለማስፍፋት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ችግሮችን ለመቅረፍና የአሰልጣኞችን ሙያዊ ብቃት ለማሳደግ ፌዴሬሽኑ በ2016 ዓ.ም በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝደንት አቶ ቢኒያም ምሩጽ በበኩላቸው የሽልማቱ ዓላማ ታደጊ ወጣቶችን ለማበረታትና ተወዳደሪ የሆኑ አትሌቶችን ለማፍራት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

በቀጣይ በጀት ዓመት ፌዴሬሽኑ አራት ፕሮጀክቶችን በመያዝ ወጣቶች በአትሌቲክሱ ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ እንሰራለን ያሉት ፕሬዘዳንቱ ከብዙ ዓመት ቡኃላ ለተመዘግበው ውጤት አስተዋጽኦ ለበረከቱ አሰልጣኞች፣የስራ አስፈጻሚ አባላት እና ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል። አትሌቶቹ የተሰጠው ዕውቅና ለበለጠ ድልና ውጤት እንዲያስመዘግቡ የሞራል ስንቅ እንደሚሆናቸው በአስተያየታቸው ገልጸው ፌድሬሽኑ ላዘጋጀው እውቅና ምስጋና አቅርበዎል። በእውቅና መርሃ ግብሩ ላይ ከወርቅ እስከ ዲፕሎማ ላመጡ አትሌቶች የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

Recent Events

Recent News

moha-soft-drinks-industry
moha-soft-drinks-industry-pepsi-cola-mobile-1.5-litre
moha-pepsi-family-party-mobile-bottles