1ኛው የታዳጊ ወጣቶች ውድድር ላይ ውጤት ላመጡ የብር ሽልማትእና የሠርተፍኬት ስጦታ ተሰጠ።

1ኛው የታዳጊ ወጣቶች ውድድር ላይ ውጤት ላመጡ የብር ሽልማትእና የሠርተፍኬት ስጦታ ተሰጠ።

ሰኔ 15/2015 ዓ.ም አዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመወከል በድሬደዋ ከተማ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባካሄደው 1ኛው የታዳጊ ወጣቶች ውድድር ላይ ውጤት ላመጡ አትሌቶች: አሰልጣኞች እንዲሁም የልዑካን ቡድን በተጨማሪም በ52ኛው የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ውድድር ውጤት ላመጡ አትሌቶች የብር ሽልማትእና የሠርተፍኬት ስጦታ ሰጠ ። በዚሁ መሰረት ወርቅ ሜዳሊያ ለአገኘ አትሌት 3000 ብር፣ የብር ሜዳሊያ ለአገኘ አትሌት 2000 ብር፣ የነሐስ ሜዳሊያ ለአገኘ አትሌት 1000 ብር፣ ዲፕሎማ ለአገኘ አትሌት 750 እንዲሁም ለተሳታፊ አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው 500 ብር የማበረታቻ ሽልማት አግኝተዋል። በሽልማት ፕሮግራሙ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ማህበራት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አያሌው ታደለ የተገኙ ሢሆን ፌዴሬሽኑ እየሠራ ያለውን በማድነቅ በቀጣይም በታዳጊ ወጣቶች ላይ ተጠናክሮ መሠራት እንዳለበት እና ቢሮም ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል:: ይህ ውጤት እንዲገኝ ለአደረጉ አሰልጣኞች፣ ቡድን መሪዎችና አስተባባሪዎች ለእያንዳንዳቸው 3000 ብር የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል።